ይህ የስልጠና ትምህርት የተለያየ ደረጃ ልምድ ላላቸው እና የተካኑ አንባቢያን ላይ ኢላማ ያደረገ፣ አንድ የማበልጸጊያ አካባቢን ለማዘጋጀት የተላያዩ አማራጮችን ይሸፍናል፡፡ በክፍል 2 ውስጥ የሚታየውን አማራጪ ለመጠቀም ከወሰናችሁ፣ አጠቃላይ የሆነ የኮምፒዩተር ዕውቀት ከመኖር በስተቀር፣ ይህንን የስልጠና ትምህርት ለማጠናቀቅ የሚያስፈልግ ምንም አይነት ቅድመ ዝግጅት አያስፈልጋችሁም፡፡ በክፍል 3 ውስጥ ያለውን (አብዛኛዎቹ አንባቢያን አንድ ወቅት ላይ እንዲሞክሩት ምክሬን የምለግስበትን) በጣም ፈታኝ የሆነውን መዋቅር ተግባራዊ ለማድረግ ከፈለጋችሁ፣ (በማዘዥያ መስመር ላይ መሰረታዊ እውቀትን ለማግኘት የሚያስፈልገውን ትምህርት ተማር ላይ እንደተሸፈነው) ከዩኒክስ የማዘዥያ መስመር ጋር አንድ መሰረታዊ የሆነ ትውውቅ ሊኖራችሁ ይገባል፤ እንዲሁም (በጽሑፍ አርታኢ ላይ መሰረታዊ እውቀትን ለማግኘት የሚያስፈልገውን ተማር ላይ እንደተሸፈነው) ከአንድ የጽሑፍ አርታኢ እና አንድ ስርዓትን ከማዋቀር ጋር ትውውቅ ሊኖራችሁ እንደሚገባ ይመከራል፡፡
የዚህ የስልጠና ትምህርት የኢ-መጽሐፍ ስሪቶች በበቂ ተማር ላይ በነጻ ይገኛሉ።