እንደገና ወደ ነበረበት ፒኤችፒ1 በይፋ ከመመለሱ በፊት፣ የቀድሞ ድርጅቴ (ሲዲ ቤቢ) የድር አሰራሩን ከፒኤችፒ ወደ ሩቢ ኦን ሬይልስ በይፋ ከቀየሩት ከመጀመሪያወቹ ውስጥ አንዱ ነበረ (ስለዚህ ታሪክ ለማንበብ የፈለገ ይጎግለኝ)። ይህን በማይክል ሃርትል የተጻፈ መጽሐፍ መሞከር እንዳለብኝ በጥብቅ አስተያየት ስለተሰጠኝ መሞከሬ ደግሞ የግድ ሆነ፤ እና ይሄ የሩቢ ኦን ሬይልስ ስልጠና መጽሐፍ ነው እኔን ወደነበርኩበት ሬይልስ በድጋሜ እንድመለስ ያበቃኝ፡፡
ምንም እንኳን ብዙ የሬይልስ መጽሓፍትን አንብቤ የነበረ ቢሆንም ሬይልስን በመጨረሻ ላይ “እንድረዳው” ያበቃኝ ግን ይህ መጽሐፍ ነው፡፡ ሁሉም ነገር በደንብ “ማለት በሬይልስ የአሰራር መንገድ መሰረት” ተሰርቷል፤ ይህም ከዚህ በፊት ያለመድኩት ዓይነት አሰራር ነበር፤ ነገር ግን አሁን ይህንን መጽሐፍ በመጠቀም፣ ከሰራሁት በኋላ ቀላል ሆኖልኛል፡፡ በተጨማሪም ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ ፈተና-መሬ ብልጸጋን የሚጠቀም ብቸኛ መጽሐፍ ነው፤ ይህ አሰራርም፣ ሊቆች እንድንተገብረው የሚያዙን የአሰራር መርህ ሲሆን ከዚህ በፊት ግን እንደዚህ በግልጽ ተብራርቶ አያውቅም፡፡ በመጨረሻም ጊትን፣ ጊትሃብን፣ እና ሃረኩን በማሳያ ምሳሌዎች ውስጥ በማካተት ጸሐፊው አንድ ትክክለኛ ፕሮጀክትን መስራት ምን እንደሚመስል አንድ ግንዛቤን ይሰጣችኋል፡፡ የስልጠናው የኮድ ምሳሌዎችም ከዛው የተለዩ አይደሉም፡፡
ግልጽ የሆነው ድርስት አቀራረቡ እጅግ ድንቅ ነው፡፡ አዳጋች ቢሆንም፣ አኔ በበኩሌ በሶስት ረጅም ቀናቶች ውስጥ፡ የሬይልስ ስልጠናውን ማለት ሁሉንም ምሳሌዎች እና በየምዕራፉ መጨረሻ ላይ ያሉትን መልመጃዎች ሰርቸ አጠናቅቄዋለሁ። (“ይሄ የተለመደ አይደለም! ብዙ አንባቢያን ስልጠናውን ለመጨረስ ረዘም ያለ ጊዜ ይወስድባቸዋል፤” ይህ የማይክል አስተያየት ነው።) ምንም ሳትዘሉ ከመጀመርያ እስከ መጨረሻው ስሩት፣ ከዚያም ከፍተኛ የሆነ ጠቀሜታ ታገኛላችሁ፡፡
ተመቻቹበት!
ዴሬክ ሲቨርስ (sivers.org) የሲዲ ቤቢ መስራች።
የሩቢ ኦንሬይልስ ስልጠና፣ ከዚህ ቀደም ብሎ ለወጣው የሬይልስ መጽሐፌ ሬይልስስፔስና፣ አብሮኝ ለሚሰራው ጸሐፊየ አውሬሊየስ ፕሮቸዝካ ብዙ ውለታ አለበት። አውሬን ሁለቱም መጻሐፍት ላይ፣ ማለት ሬይልስስፔስ መጽሐፍ ላይ ስላደረገው ነገር እና በተጨማሪም ለዚህ መጽሐፍ ስላደረገው አስተዋጻኦ ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡ የሁለቱን የሬይልስስፔስ እና የሩቢ ኦን ሬይልስ ስልጠና አዘጋጁዋን ዴብራ ዊሊያምስ ካውሌይንም፣ በተጨማሪ ማመስገን እፈልጋለሁ፤ እሷ ወደ ቤዝቦል ጨዋታ እስከወሰደችኝ ድረስ፣ ለሷ መጽሐፍ መጻፌን እቀጥላለሁ፡፡
አንድ ረዘም ባለ ዝርዝር ውስጥ፣ ለአመታት ያስተማሩኝን እና ወኔየን ላነሳሱት የሩቢ ሊቆችን ማስተዋወቅ እፈልጋለሁ፡- ዴቪድ ሄንማየር ሃንሰን፣ የሁዳ ካትዝ፣ ካርል ሌርች፣ ጀረሚ ኬምፐር፣ ሸቬር ኖሪያ፣ ሪያን ቤትስ፣ ጀፈሪ ግሮሰንባች፣ ፔተር ኩፐር፣ ማት አይሞንቴ፣ ማርክ ቤትስ፣ ግሬግ ፖላክ፣ ዋይኔ ኢ. ሰጉይን፣ ኤሚ ሆይ፣ ዴቭ ኬሊምስኪ፣ ፓት ማዶክስ፣ ቶም ፕሬስቶን-ወርነር፣ ክሪስ ዋንስትራት፣ ቻድ ፎውለር፣ ጆሽ ሱሰር፣ ኦቤ ፈርናንዴዝ፣ አያን ማክፋርላንድ፣ ስቴቭ ብሪስቶል፣ ፕራቲክ ኔክ፣ ሳራ ሜይ፣ ሳራ አለን፣ ወልፍሬም አርኖልድ፣ አሌክስ ቻፌ፣ ጊልስ ቦውኬት፣ ኤቫን ዶርን፣ ሎንግ ኑግየን፣ ጀምስ ሊንደንባውም፣ አዳም ዊጊንስ፣ ቲክሆን በርንስማን፣ ሮን ኤቫንስ፣ ዌት ግሪን፣ ማይለስ ፎሬስት፣ ሳንዲ ማት፣ ርያን ዴቪስ፣ አሮን ፓተርሶን፣ አጃ ሃመርሊ፣ ሪቻርድ “ሽኒምስ” ሽኔማን፣ በፒቮታል ላብስ ውስጥ የሚሰሩ ጥሩ ተባባሪያን፣ የሃረኩ አጋሮቸ፣ የቶውትቦት ጉዋዶቸ እና የጊትሃብ ባልንጀሮቸ ናቸው።
ሙያዊ ገምጋሚው አንድሬ ታይን፣ የመጽሐፉ የመጀመሪያውን ጽሑፍ ጠንቅቆ በማንበብ እና ጠቃሚ ሃሳቦችን ስለለገሰልኝ ላመሰግነው እወዳለሁ። በተጨማሪም ለበቂ ተማር ሽርኮቸ ኒክ መርዊን እና ሊ ዶናሆ‘ን ይሄን የስልጠና መጽሐፍ ለማዘጋጀት ስለ ሰጡኝ ድጋፍ ሁሉ ላመሰግናቸው እወዳለሁ።
በመጨረሻም፣ እጅግ በጣም ብዙ አንባቢዎች (ሁሉንም እንዳልዘረዝራቸው ከቁጥር በላይ ናቸው)፣ ይህ መጽሐፍ በሚጻፍበት ጊዜ በጣም ብዙ የስህተት ዘገባወችን እና ሃሳቦችን ሰተዋል፤ ስለዚህም እኔ ይህ መጽሐፍ ይሄን ያህል ግሩም መጽሐፍ መሆን እንዲችል ስላደረጉት እርዳታ አመሰግናቸዋለሁ፡፡
ማይክል ሃርትል ለድር ማበልጸጊያ ማስተዋወቂያ መሪነቱን ከያዙት መካከል አንዱ የሆነውን የሩቢ ኦንሬይልስ ስልጠናን የፈጠረ እና እንዲሁም የለበቂ ተማር መስራች እና ዋና ጸሐፊ ነው። ካሁን በፊት ትምህርትን በበላይነት በማስተማር አንድ የእድሜ ልክ የስኬት ሽልማት በወሰደበት በካሊፎርኒያ ቴክኖሎጅ ተቋም (ካልቴክ) ውስጥ የፊዚክስ አስተማሪ ነበረ። የሃርቫርድ ኮሌጅ ምሩቅ ነው። ከካልቴክ በፊዚክስ ፒኤች.ዲ ሲኖረው የዋይ ኮምቢናቶር የስራ ፈጣሪ ፕሮግራምም ምሩቅ ነው።
የሩቢ ኦንሬይልስ ስልጠና:- ድር ማበልጸግን በሬይልስ ተማር መጽሐፍ የቅጅ መብት © በማይክል ሃርትል 2016። መጨረሻ የቅጅ መብቱ የዘመነበት ቀን 2021/11/26 11:29:55 በፓስፊክ ጊዜ አቆጣጠር2 ነው።
ሁሉም የሩቢ ኦንሬይልስ ስልጠና ውስጥ ያሉት የኮድ ምንጮች በ‘ማ.ቴ.ተ (MIT) (በ‘ማሳቹሴትስ የቴክኖሎጂ ተቋም) ፈቃድ እና በ‘ቢራጋብዘኝ ፈቃድ ጥምረት ስምምነት መሰረት፣ ሁሉንም የኮድ ምንጮች ማግኘት ይቻላል። አስተውሉ! ይህ ማለት ሁለቱም ፈቃዶች ትክክለኛ ናቸው ማለት ነው። በሶፍትዌሩ የማ.ቴ.ተ ፈቃድ መሰረት፣ ሶፍትዌሩን ለመጠቀም ከፈለጋችሁ፣ እኔን ቢራ መጋበዝ አያስፈልግም ማለት ነው።
የ`ማ.ቴ.ተ ፈቃድ
የቅጅ መብት (ሲ) 2016 ማይክል ሃርትል
የዚህን ሶፍትዌር ቅጅ እና ተዛማጅ ሰነዶቹን ለሚያገኝ ለማንኛውም ተጠቃሚ ያለክፍያ እንዲጠቀም
ተፈቅዷል። ይህም ያለገደብ በሶፍትዌሩ ለመጠቀም፣ ለመቅዳት፣ ለማሻሻል፣ ከሌላ ኮድ
ጋር ለማዋሃድ፣ ለማሳተም፣ ለማከፋፈል፣ ለሌሎች ፈቃድን ለመስጠት እና ወይም የሶፍትዌሩን ቅጅ
ለመሸጥ የሚቀመጡ ገደቦችን ባለማካተት እና ሶፍትዌሩን ለሚያቀርበው ሰው ፈቃድ እና መብት
በመስጠት ነው። በሚከተሉት ሁኔታዎችም ተገዥ ይሆናል:-
ከዚህ በላይ ያለው የቅጂ መብት እና የዚህ ፈቃድ ማስታወቂያ፣ በሁሉም የሶፍትዌሩ ቅጅዎች
ወይም ዋና ዋና ክፍሎች ውስጥ መካተት አለበት።
ሶፍትዌሩ ``ልክ እንደዚህ እንዳለ'' ቀርቧል፣ ማለት ያለምንም ዓይነት ዋስትና፣ በግልጽ ወይም በተዘዋዋሪ፣
በንግድ ፈቃድ ሳይወሰን ነገር ግን ዋስትናውን በማጠቃለል፣ ለተወሰነ ተግባር በማዋል እና ህግን
ባለመጣስ ነው። በማንኛውም ዓይነት ክስ፣ ጥፋት ወይም ለሌላ ተጋላጪነት፣ በስምምነት ድርጊት ውስጥ፣
ስህተት ወይም ሌላ ነገር፣ በሚነሱ ነገሮች፣ ከሶፍትዌሩ ጋር በሚገናኝ ወይም በማይገናኝ ነገር ወይም
በሶፍትዌሩ ውስጥ ለሚደረጉ ለማንኛውም አጠቃቀሞች ጸሐፊው ወይም የቅጅ መብት ባለቤቱ ተጠያቂ
የሚሆንበት ሁኔታ የለም።
የ`ቢራጋብዘኝ ፈቃድ (ክለሳ 42)
ማይክል ሃርትል ይህንን ኮድ ጽፏል። ይህንን ማስታወቂያ እስከያዛችሁበት ጊዜ ድረስ በዚህ መጽሐፍ
የፈለጋችሁትን ነገር ልታደርጉ ትችላላችሁ። ይህ በንዲህ እያለ፣ አንድ ቀን ከተገናኘን እና መጽሐፉ
የሆነ ስጦታ ይገባዋል ብላችሁ ካሰባችሁ፣ አንድ ቢራ ልትጋብዙኝ ትችላላችሁ።